ይህም ከደማስቆ ጋር እንደ አዲስ እንድንጀምር ያደርጋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከደማስቆ ጋር እንደ አዲስ መጀመር ስለሚፈልጉ አሜሪካ በሶሪያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ለማስወገድ እያጤኑበት መሆኑን መናገራቸውን አናዶሉ ዘግቧል።
ትራምፕ ታህሳስ ወር ላይ የአሳድ መንግስት ከተወገደ በኋላ ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ጋር በሶሪያ ስለተጣለዉ የአሜሪካ ማዕቀብ መነጋገራቸዉን ገልጸዋል፡፡
በወቅቱም ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አሜሪካን በሶሪያ ላይ የጣለችዉን ማዕቀብ እንድታነሳ ጠይቀዋቸዉ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
እኛ ማዕቀብ ያደረግንበት መንገድ በእውነቱ ብዙ አዲስ ጅምር የሚሰጣቸዉ አይደለም፤ ስለዚህ እነሱን ልንረዳቸው እንደምንችል ማየት እንፈልጋለን ። ዉሳኔዉንም በቁርጠኝነት ለመፈጸም እንሞክራለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በፕሬዝዳንቱ የተሰጡት መግለጫዎች ምዕራባውያን በሶሪያ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ በቅርቡ ሊያነሱት እንደሚችሉ የቅርብ ጊዜ ማሳያዎች ናቸው።
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የአውሮፓ ህብረት በሶሪያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ቀስ በቀስ እንደሚያነሳ ባለፈዉ ሳምንት መናገራቸዉ ይታወሳል፡፡
እስከዳር ግርማ
ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
