ባለፉት 3 ዓመታት ከ 3 መቶ 17 ሺህ በላይ ኢትዮጲያዊያን ስደተኞችን ወደ ሃገር ውስጥ መመለስ መቻሉን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነዉ የገለጸዉ፡፡
ከመጋቢት 2014 እስከ ሚያዚያ 2017 ባለው 3 አመታት ከ 3 መቶ 17 ሺህ 1 መቶ 94 በላይ ኢትዮጲያዊያን ስደተኞችን ወደ ሃገር ውስጥ መመለስ መቻሉን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡
ከሳውዲ አረቢያ፤ የመን ፤ ሱዳን ፤ ኦማን እና ሊባኖስ ከተውጣጡ ሃገራት ከተመለሱት ዜጎች ውስጥ 8 ሺህ 5መቶ56ቱ ህፃናት መሆናቸውም በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
ከተመላሾቹ መካከል 2 መቶ 19 ሺህ የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ፤ 32 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች ናቸዉ፡፡
ሕጋዊ በሆነ እና ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ከሀገር የሚወጡ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነዉ የተባለ ሲሆን፤በተመሳሳይ ደግሞ ወደ ሀገር ውስጥ የሚመለሱ ዜጎች ቁጥርም ከፍተኛ መሆኑ ተነስቷል፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
