የአስቸኳይ ፖስፖርት ኦንላይን ሲስተም የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎበት ስራ መጀመሩን ተገለፀ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለአዲስ አበባ አስቸኳይ ፓስፖርት አመልካቾች ፤የአስቸኳይ ፖስፖርት ኦንላይን ሲስተም የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎበት ስራ መጀመሩን አስታውቋል።

ከግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ሁሉም አመልካች በኦንላይን በማመልከት በቀጠሮ ቀን ብቻ ወደ ተቋሙ መሄድ እና መስተናገድ እንደሚቻል አሳውቋል።

በኦን ላይን መሙላት ያልቻሉ አስቸኳይ ጉዳይ ያላቸው አመልካቾች በአካል መጥተው መስተናገድ እንደሚችሉም ገልጿል።

በተጨማሪ አገልግሎቱ ” ከግንቦት 6/ 2017 ዓ/ም ጀምሮ መደበኛ የፓስፖርት አገልግሎት ከጠዋቱ 12:00 – 8:00 ሰአት ድረስ የአስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎት ደግሞ ከ9:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4:00 ሰአት በሁለት ፈረቃ
እንደሚሰጥ አስታውቆ፤ተገልጋዮች በቀጠሯቸው ቀን ብቻ ወደ ተቋሙ በመምጣት ተስተናገዱ ብሏል።

ከቀጠሮ ቀን ውጭ በተቋሙ አካባቢ መቆምም ሆነ አላስፈላጊ እንቅስቃሴ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው ” ሲልም አሳስቧል።

ግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *