እስራኤል በአንድ ምሽት ባደረሰችዉ ጥቃት 41 ፍልስጤማዊያን ህይወታቸዉ ማለፉ ተገለጸ፡፡

ጥቃቱ በመኖሪያ ቤቶች እና በጋዛ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ላይ የደረሰ ነዉ፡፡

እንደ ህክምና ባለሙያዎች ገለጻ ካን ዩኒስ በከፍተኛ የእስራኤል ጥቃት የተጎዳች ሲሆን፤36 ሰዎችም ህይወታቸዉ አልፏል፡፡

እስራኤል በጦር አዉሮፕላኖች ባደረሰችዉ ጥቃት ደግሞ በአንድ ምሽት በጋዛ በአጠቃላይ 41 ተፈናቃይ ፍልስጤማዊያን በቤታቸዉ እና በመጠለያ ካምፖች ህይወታቸዉ ማለፉ ተገልጿል፡፡

ንጋት አከባቢ በካን ዩኒስ በሚገኙ ቤቶች እና መጠለያ ካምፖች በደረሰ የአየር ጥቃት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ 36 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ፤ በሰሜናዊ ጋዛ በተፈጸመ ሌላ ጥቃት ደግሞ 5 ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል፡፡

ጥቅምት 2023 በጀመረዉ ጥቃት ከፍተኛዉ ቁጥር ሴቶች እና ህጻናት የሆኑ 53ሺህ የሚጠጉ ፍልስጤማዊያን ህይወታቸዉ አልፏል፡፡

እስራኤል በጋዛ እያደረሰች ባለችዉ ጥቃት በዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ቀርቦባታል፡፡

እስከዳር ግርማ

ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *