የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔትያናሁ ሃማስ ታጋቾችን በሙሉ ለቆ ትጥቁን የሚፈታ ከሆነ ሀገራቸው በጋዛ የጀመረችውን ዘመቻ ልታቆም እንደምትችል አስታወቁ።

ኔትያናሁ ይህን ያሉት እንግሊዝ ፣ ፈረንሳይ እና ካናዳ እስራኤል በጋዛ የጀመረችውን አዲሱን ዘመቻ እንድታቆም ማስጠንቀቂያ ከሰጡ በኋላ ነው።

የብሪታንያው ጠቅላይ ሚንስትር ኪር ስታርመር ፣ የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ማርክ ካኒ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የጀመረችውን አዲሱን ዘመቻዋን ካላቆመች ማዕቀብ ሊጥሉ እንደሚችሉ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስጠንቅዋል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔትያናሁ ለመሪዎቹ በሰጡት ምላሽ ግን “ምዕራባዉያን የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን መንገድ ተከትለው እስራኤልን ቢደግፉ ይሻላል” ብለዋል።

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የጀመረችውን ዘመቻ ለማቆምም “ሐማስ የቀሩ ታጋቾችን ከለቀቀ፣ ትጥቁን ከፈታ እና መሪዎቹ ጋዛን ለቀው የሚሰደዱ ከሆነ ብቻ ነው ” ፤ ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ለኢራን ሲሰልሉ ነበር ያለቻቸው ሁለት ዜጎቿን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታዉቃለች።

የእስራኤል የደህንነት ባለስልጣናት እንዳሉት ሁለቱ የ24 ዓመት ዕድሜ እንዳላቸው የተነገረላቸው እስራኤላዉያን ወጣቶች ከኢራን ተልዕኮ ተቀብለው በእስራኤል ምድር ሲሰልሉ ነበር ።

በጣቶቹ በተለይ በደቡባዊ እስራኤል በሚገኙት የክፋር አሂም ማህበረሰብ ውስጥ የእስራኤሉን የመከላከያ ሚኒስቴር እስራኤል ካትስን ስም የማጥላላት ክስም ቀርቦባቸዋል።

ወጣቶቹ ከኢራን ባለስልጣናት ተሰጣቸው በተባለው ተልዕኮ መሰረት በማህበረሰቡ ውስጥ በቀጥታ የቪዲዮ ስርጭት ሚኒስትሩን ሲሳደቡ እና ሲያጥላሉ ተደርሶባቸዋል ነው የተባለው።

በቅጥጥር ስር ስለዋሉ ወጣቶች እና ስለቀረበባት ክስ ግን ኢራን ያለችው ነገር የለም።

ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *