ሩስያ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በዩክሬን ላይ በበርካታ ድሮኖች የታገዘ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ ብሪታንያ እስከ 100 የሚደርሱ ማዕቀቦችን መጣሏን አስታውቃለች።
አዲሱ የሩስያ ማዕቀብ ” ለሩሲያ ወታደራዊ ቁሶች ማምረቻ ድጋፍ የሚሰጡትን ” ጨምሮ “የኃይል አቅርቦት በመላክ እንዲሁም ለመረጃ ጦርነት ድጋፍ በሚያደርጉ ” አካላት ላይ ያነጣጠረ መሆኑን የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የብሪታንያ በሩሲያ ላይ ዘርፈ ብዙ ማዕቀብ መጣል የተሰማው የቅርብ አጋሯ የአውሮጳ ህብረት “በዩክሬን የተቀናጀ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችል ” ነው ያለውን ማዕቀብ ለ17ኛ ጊዜ መጣሉን ካስታወቀ በኋላ ነው ።
ብሪታንያ በትላንትናው አዲሱ የማዕቀብ ማዕቀፏ ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ ለሩስያ ድጋፍ ሲያደርጉ ነበሩ የተባሉ “የፋይናንስ ተቋማትንም ” እንደሚመለከት የሚኒስቱሩን መግለጫ ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ከብሪታንያ እና ከህብረቱ አዲስ የማዕቀብ ማዕበል የተጣለባት ሩስያ ለርምጃው ለጊዜው መልስ አልሰጠችም ። ባለፈው ቅዳሜ ሩስያ በዩክሬን የተለያዩ ከተሞች የ273 ድሮኖች ጥቃት መፈጸሟን ዘገባው አመልክቷል።
ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም
