አሜሪካ “ጎልደን ዶም” ስትል የሰየመችው እና የወደፊቱ የሚሳዔል መቃወሚያ የተባለውን ዲዛይን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ይፋ አድርገዋል ።
“ቀጣዩን ትውልድ” ለመከላከል በሚል ተግባራዊ በተደረገው አዲስ የሚሳዔል መከላከያ እቅድ አካል ለመሆን ካናዳ ንግግር ላይ መሆኗ ተነግሯል።
25 ቢሊየን ዶላር መነሻ ገንዘብ ለተግባራዊነቱ እንደሚያስፈልግ ለተነገረለት ለዚህ እቅድ የማርክ ካርኒ መንግስት ከዋሽንግተን ጋር ብርቱ ንግግር በማድረግ ላይ ነው ተብሏል።
ሆኖም ይህን ሁሉን አቀፍ ስርዓት አሜሪካ እንዴት ተግባራዊ ታደርገዋለች በሚለው እና የካናዳ ተሳትፎ ላይ ጥርጣሬ ስለመኖሩ የዘርፉ ባለሙያዎች መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
“ጎልደን ዶም” የተሰኘው የሚሳዔል መከላከያ ስርዓት ዶናልድ ትራምፕ የሥልጣን ዘመናቸው ከማብቃቱ በፊት አገልግሎት ላይ ይውላል ተብሏል።
ሰንፔር እንዳለው
ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም
