ናፖሊ ከ ካግሊያሪ እና ኢንተር ሚላን ከ ኮሞ በተመሳሳይ ምሽት 3፡45 ላይ ይገናኛሉ።
ናፖሊ በአንድ ነጥብ ልዩነት ሊጉን እየመራ በሜዳው አርማንዶ ማራዶና ስቴዲየም የሚያደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ከሁለት ዓመት በኋላ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል።
ኢንተር ሚላን ከናፖሊ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በሴስክ ፋብሪያስ ከሚሰለጥነው ኮሞ ጠንካራ ፈተናም ይጠብቀዋል።
ኢንተር ሚላን በተከታታይ ሻምፒዮን ለመሆን የራሳቸውን የቤት ስራ አጠናቀው የናፖሊን መሸነፍ ወይም ነጥብ መጣል ይጠብቃሉ።
ናፖሊ ተሸንፎ ኢንተር ሚላን አቻ የሚወጣ ከሆነ የ2024/25 አሸናፊን ለመለየት ሁለቱ በድኖች 39 ሳምንት እርስ በርስ አንድ የመጨረሻ ጨዋታ የሚያደርጉም ይሆናል።
የጣሊያን ሴሪ ኤን ናፖሊ በ79 ነጥብ ሲመራ ኢንተር ሚላን በ78 ነጥብ ይከተላል።
ጋዲሳ መገርሳ
ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም
