አሜሪካ ከአገሯ የምታባርራቸውን ስደተኞች በሩዋንዳ ለማስፈር እየተደራደረች መሆኗ ስጋት እንደፈጠረባቸው የመብት ተሟጋቾች እየገለፁ ነው፡፡

ባለፈው አመት ዩናይትድ ኪንግደም፣ ጥያቄያቸው ያልተሳካላቸው ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለማስወጣት የያዘችው እቅድ ከተሰረዘ በኋላ፣ ኪጋሊ ከአሜሪካ ጋር እየተደራደረችበት ያለው ተመሳሳይ ጉዳይ በመብት ተሟጋቾች ዘንድ ስጋትን አጭሯል፡፡

አሜሪካ ከአገሯ የሚባረሩ ህገወጥ ሰዎችን በሩዋንዳ ለማስፈር ንግግር መጀመሯና የሩዋንዳ መንግስትና የትራምፕ አስተዳደር በዚህ ጉዳይ ላይ እየተደራደሩ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

የሩዋንዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኦሊቨር በያዝነው ወር ሃገራቸው ከዋሺንግተን ጋር መደራደሯን አረጋግጠው ዝርዝር መረጃዎች ወደፊት ይፋ እንደሚደረጉ ገልፀዋል፡፡

የዶናልድ ትራምፕ መንግስት ስደተኞችን ወደ 3ተኛው የዓለም ሃገራት እያባረረ ይገኛል፡፡ ለአብነትም ወደ ኤል ሳልቫዶር የሚጠረዙ ሰደተኞቸ ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

ይባስ ብሎ ዋሺንግተን በጦርነትና አለመረጋጋት ከምትታመሰው ሊቢያ ጋር በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን በተመለከተ ተደጋጋሚ ንግግሮችን እያደረገች ስለመሆኗ ነው የተዘገበው፡፡

ይህ የአሜሪካ ተግባር ታዲያ ስጋት ፈጥሮብናል ሲሉ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ድምፃቸውን እያሰሙ ይገኛሉ ሲል አልጀዚራ ዘግቧል ፡፡

አዲስዓለም አበበ

ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *