በ38ተኛ ሳምንት መርሐግብሮች የሊጉን አሸናፊነት ቀድሞ ያረጋገጠው ሊቨርፑል በአመቱ የሰበሰባቸውን ነጥቦች ሰማንያ አራት አድርሷል።
ማንችስተር ዩናይትድ በአርባ ሁለት ነጥቦች አስራ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቅ በታሪኩ አስከፊውን የውድድር አመት አሳልፏል።
አርሰናል ለተከታታይ ሶስተኛ የውድድር ዘመን ሊጉን ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።
ቼልሲ ማሸነፉን ተከትሎ የአውሮ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን በመያዝ አጠናቋል።
ግብፃዊው የሊቨርፑል ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በ 28 ጎሎች የሊጉ ከፍተኛ ግብ አግቢ በመሆን አጠናቋል።
መሐመድ ሳላህ በአንድ የውድድር አመት 47 ግቦች ላይ ተሳትፎ በማድረግ በአንዲ ኮል እና አለን ሺረር ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ተጋርቷል።
በሻምፒየንስ ሊግ :- ሻምፒየኑ ሊቨርፑል ፣ አርሰናል ፣ ማንችስተር ሲቲ ፣ ቼልሲ ፣ ኒውካስል ዩናይትድ እና ቶተንሀም
በዩሮፓ ሊግ :- አስቶን ቪላ እና ክሪስታል ፓላስ
በኮንፈረንስ ሊግ :- ኖቲንግሃም ፎረስት እና ብራይተን ይሳተፋሉ።
የአመቱ የወርቅ ጓንት አሸናፊዎች ተለይቷል እስከ መጨረሻው ሳምንት በዘለቀው በዚህ ፉክክር ዴቪድ ራያ እና ማትዝ ሴልስ ሽልማቱን የሚጋሩት ይሆናል።
ሁለቱ ግብ ጠባቂዎች በዘንድሮው የውድድር ዘመን በአስራ ሶስት ጨዋታዎች ላይ ግብ ሳይቆጠርባቸው መውጣት ችለዋል።
ሌስተር ሲቲ፣ ኢፕስዊች ታውን እና ሳውዝሀምፕተን ከሊጉ የወረዱ ክለቦች ሆነዋል።
ሊድስ ዩናይትድ ፣ሰንደርላንድ እና
በርንሌይ ቀጣይ አመት በእንግሊዝ ፕርሚየር እንመለከታቸዋለን።
ጋዲሳ መገርሳ
ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም
