በ9 ወራት አፈፃፀም ዉስጥ ማህበረሰብን በአግባቡ ባለማስተናገድ ጉድለት የነበረባቸዉን 366 የሚሆኑትን የፓሊስ አባላት መጠየቃቸዉን ኮምሽኑ አሳስታውቋል
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ከኢትዩ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቁይታ እንዳሉት የፖሊስ ኮምሽኑ የቅርብ ጊዜ ሪፖርት በመዲናይቱ ከባድ ወንጀሎች 45 በመቶ ቀንሶ መታየቱን ገልፅዋል።
በ11ዱም ክፍለከተማ 119 ወረዳዎች እና 833 ቀጠናዎች ለሚገኘዉ ነዋሪ የከተማዉ ነባራዊ ሁኔታን መነሻ በማድረግ የግንዛቤ ማስጨብጫ ስራዎች ተሰርቷል ብለዋል።
በከተማይቱ ወንጀል ይፈፀምባቸዋል ተብለዉ በሚገመቱ ቦታወች ላይ 440 ካሜራወች መተከላቸዉን የተተከሉ ካሜራዎች የወንጀል መከላከል ሥራን እያገዙ ነዉ ተብሏል።
በተመሳሳይ በተቋሙ ያሉ እነዚህ መሳሪያዎች የተቋሙን አባላት ከተጠርጣሪዎች አያያዝ እና የህግ አግባብን የተከተለ የምርመራ መደረግ አለመደረጉን የሚያሳይ እንዲሆን የተዘጋጀ መሆኙን ኮምሽኑ ገልፀዋል።
እነዚህ ስራወች እየተሰሩ ያሉት በ 11 ክፍለ ከተሞችና እንዲሁም በ90 ፓሊስ ጣቢያወችና በ832 የማህበረሰብ አቀፍ የፓሊስ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ስራወቹ እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፅዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
