የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን አትሌት ገለቴ የገጠማት ችግር ለመፍታት እና እልባት እንዲያገኝ በሁሉም ጉዳይ እንደሚሰራ ገልፀዋል ።
በሴት አትሌቶች ላይ የሚስተዋለው ጥቃት ቀላል የሚባል እንዳልሆነና አትሌቷ ወደ ሚዲያ ወጥታ የገጠማትን ችግር ተናገረች እንጂ ለሀገራቸው ብዙ ዋጋ ከፍለው ብዙ ችግር ውስጥ ያሉ አትሌቶች እንዳሉ ተናግሯል ።
የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሰረት ደፋር ከመጀመርያው አንስቶ የገጠማት ችግር ሰፊ መሆኑን በማንሳት ለሀገሯ ስም እና ዝና የከፈለችው መስዋዕትነት ትልቅ መሆኑንና ትክክለኛውን ፍትህ እንዲሰጣት ጠይቀዋል ።
የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ምሩፅ የመገናኛ ብዙሃን በሴት አትሌቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ለመከላከል ከፌዴሬሽኑ ጎን በመሆን እንዲሰሩ ጠይቀዋል ።
የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ተወካዮች ሌተናል ኮነሬል አትሌት የማነ ፀጋይ እና አትሌት በላይነሽ ኦልጅራ አትሌቶችን እንደገንዘብ ምንጭ አድርጎ መጠቀም ጉዳዩን ውስብስብ እንዳደረገው እና መንግስት ጨምሮ ሁሉም አካላት እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል ።
የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የሕክምና ባለሙያ ዶ/ር አያሌው ጥላሁን የአትሌቶች ሁለንተናዊ ጥበቃ ፖሊሲ በኢትዮጵያ እንዲተገበር እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ የአትሌቶችን ጥበቃ የሚደነግጉ ሕጎች ከ2023 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆኑ ውሳኔ ማሳለፋንና የአትሌቶች ሁለንተናዊ ጥበቃ ፖሊሲ በኢትዮጵያ እንዲተገበር እየተሰራ መሆኑን መናገራቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
ሰኔ 3 ቀን 2017 ዓ.ም
