የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዝንጀሮ ፈንጣጣ (ኤምፖክስ) የተያዙ ሰዎች ቁጥር 18 መድረሱን አስታወቀ።

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን ባወጡት መግለጫ እስከ ሰኔ 4 2017 ዓ.ም. ድረስ ብቻ 18 በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ (ኤምፖክስ) ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ መከሰቱ ይፋ የሆነው ግንቦት 17/ 2017 ዓ.ም. ሲሆን በበሽታው ከተያዙት መካከል የአንድ ወር ጨቅላ ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እስከ ትናንት ሰኔ 04/ 2017 ዓ.ም. ድረስ 102 ለሚሆኑ የላቦራቶሪ ምርመራዎች ማድረጉን እና በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች ቁጥር 18 መድረሱን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

እስካሁን በበሽታዉ ከተያዙት 18 ሰዎች መካከል አምስቱ ሙሉ በሙሉ ማገገማቸው ተገልጿል።
የመጀመርያው የኤምፖክስ ታማኣሚ የተገኘው ግንቦት 16/ 2017 ዓ.ም. በኦሮምያ ክልል ሞያሌ ከተማ መሆኑ ይታወሳል።

እንደ ጤና ጥበቃ መረጃ ከሆነ የኤምፖክስ ቫይረስ የተለያዩ ዝርያዎች ያሉት ሲሆን በኢትዮጵያ በሕክምና ላይ ካሉ ታማሚዎች የተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ የዘረመል ምርመራ በተገኘው ውጤት መሰረት ክሌድ 1 ቢ (Clade 1b) የተባለው ዝርያ ዓይነት እንደሆነ ለማረጋገጥ ተችሏል።

ይህ የቫይረስ ዝርያ በአንጻሩ ከፍተኛ የሚባል የስርጭት መጠን ያለውና በዚህ የቫይረስ ዝርያ ከበሽታው ጋር በተያያዘ የሚከሰት የሞት መጠን በአንፃሩ ከፍተኛ እንደሆነ በሌሎች አገራት የተገኘ ልምድ ያሳያል።

ለኤምፖክስ በሽታ አጋላጭ ሁኔታዎች ተብለው ከተለዩት መንገዶች መካከል በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር የሚደረግ የሰውነት ንክኪ፣ የግብረ ስጋ ግንኙነት እንዲሁም ከታማሚ ሰው ጋር ንክኪ ያለውን ቁስ በጋራ መጠቀም በዋነኛነት ይጠቀሳሉ።

በኢትዮጵያ በሽታው መያዛቸው ለመጀመርያ ጊዜ የተገለፀው በሞያሌ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የ21 ቀን ዕድሜ ያለው ሕጻን እና እናቱ ነበሩ።

ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *