ሀይቁ በስምንት አመት ጊዜ ዉስጥ 65 ኪ.ሜ ተጉዞ አሁን ላይ በወረዳዉ ዋና ከተማ ለመድረስ ጥቂት ኪሎ ሜትሮች መቅረቱን ሰምተናል።
የዉሃ መጥለቅለቁ ለዋና ከተማዉ ኦሞራቴ ስጋት መፈጠሩ የተገለፀ ሲሆን ለከተማዉ ነዋሪዎች ፍርሃት ፈጥሯል ተብሏል።
የኦሞ ወንዝ እና የቱርካና ሀይቅ ሙላት ተደጋጋሚ አደጋን በዳሰነች ወረዳ ላይ እያስከተለ እንደሚገኝ ይገለፃል።
በአካባቢው በከፍተኛ ሁኔታ የመሬት መሰንጠቅ አደጋ እየተከሰተ መሆኑ ደግሞ ለኦሞራቴ ከተማ ስጋት መደቀኑ ከወረዳዉ የተገኘ መረጃ ያሳያል።
ከኢትዮ አፌም ጋር ቆይታ ያደረጉት የደቡብ ኦሞ ዞን አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ምክትል ኃላፊ አቶ ሎክኛንጋ ሙርሌ ዉሃዉ ወደ ከተማ እንዳይገባ ግድብ እየተሰራ መሆን ተናግረዋል።
79 ሺህ 828 የህብረተሰብ ክፍሎች ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ተጠልለዋል ተብሏል።
የደብብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮምኒኬሽን እንደገለፀዉ መረጃ በባለፋት የክረምት ጊዜያት የዉሃዉ ሙላት በወረዳዉ 28 ቀበሌያትን መፈናቀሉን ያሳያል።
አያይዞም በባለፉት ጊዜያት ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉት ነዋሪዎች አሁን ላይ በሶስት ቦታዎች በጊዜያት እንዲጠለሉ መደረጉን መረጃዉ ገልፆል።
እየታየ የሚገኘዉ የነዋሪዎች ሽሽት እና ዳግም መፈናቀል በሰፈሩባቸዉ አካባቢዎች ሊያገኟቸዉ የሚገቡ የሰብአዊ አገልግሎት ከማዳረስ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ የዞኑ አደጋ ስጋት ነግሮናል።
ቁምነገር አየለ
ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም
