ማርኮ ሩቢዮ አሜሪካዊያን ከሞስኮ ጋር ገንቢ ግንኙነት ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩሲያውያንን በሩሲያ ቀን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ሩሲያውያንን በሩሲያ ቀን እንኳን ደስ አላችሁ በማለት፤ አሜሪካውያን ከሞስኮ ጋር ‹‹ገንቢ ግንኙነት ለማድረግ››ያላቸውን ቁርጠኝነት አጽንኦት ሰጥተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋሽንግተን ከክሬምሊን ጋር ፍሬያማ ግንኙነት ለማድረግ ያላትን ፍላጎት
አረጋግጣለሁ፤የሩሲያ ዜጎች ለብሩህ የወደፊት ተስፋ ያላቸዉን ፍላጎትም እደግፋለሁ ብለዋል፡፡

በተጨማሪም አሜሪካ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ከሩሲያ ፌዴሬሽን ጋር ገንቢ ግንኙነት ለማድረግ ያላትን ፍላጎት በድጋሚ እናረጋግጣለን ብለዋል፡፡

ሩቢዮ፤ሰላም መኖሩ በዋሽንግተን እና በሞስኮ መካከል የበለጠ የጋራ ተጠቃሚነት ግንኙነትን እንደሚያሳድግ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከጥር ወር ጀምሮ በርካታ የስልክ ልዉዉጦችን አድርገዋል።

የሁለቱም ሀገራት ልዑካን በየካቲት ወር ኢስታንቡል ውስጥ ተገናኝተው የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች አሠራርን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መምከራቸዉ ይታወሳል፡፡

እስከዳር ግርማ

ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *