የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የአባሉን ያለመከሰስ መብት አነሳ

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የአቶ ዓለማየሁ ጢሞቲዮስን ያለመከሰስ መብት ገፈፈ ። ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ባካሄደው 6ኛ ዙር 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው ፡፡

ምክር ቤቱ የአቶ ዓለማየሁን ያለመከሰስ መብት የተነሳው በሥልጣን ያለ አግባብ መጠቀም ፣ በኮንትሮባንድ ፣ በህገ ወጥ የጦር መሣሪያ እና በአደንዛዥ ዕጽ ዝውውር ተሳትፈው በመገኘታቸው ነው ሲል የክልሉ ፍትህ ቢሮ ለምክር ቤቱ አስረድቷል ፡፡

ምክር ቤቱ በፍትህ ቢሮ ሃላፊው የቀረበለትን ዝርዝር ካዳመጠ በኋላ ያለመከሰስ መብታቸውን ለማንሳት የቀረበለትን አጀንዳ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

ያለመከሰስ መብታቸው በምክር ቤቱ የተነሳው አቶ ዓለማየሁ ጢሞጢዎስ ላለፉት አምስት ዓመታት የክልሉን ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በሃፊነት አገልግለዋል ፡፡

ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *