የሱዳን የፈጥኖደራሽ ሃይል ከሱዳን ጦር ጋር እደረገ ባለው ውጊያ በማፈግፈግ ሃገሪቱ ከግብፅ እና ከሊቢያ ጋር የምትዋሰንበትን ስትራቴጂካዊ ድንበር አካባቢ መቆጣጠሩን ተናግሯል።
የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ እንዳሉት አማፂ ቡድኑ ሱዳንን፣ ሊቢያን እና ግብጽን የሚያገናኘውን ቁልፍ ስፍራ በውጊያ መያዙን ተናግረዋል።
በተደረገው ውጊያም የሱዳን ጦር በሰውና በመሳሪያ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት ተናግሯል።
የሱዳን ጦር የሊቢያን ወታደራዊ አዛዥ ካሊፋ ሃፍታርን የፈጥኖደራሽ ሃይሉን ይደግፋሉ ሲል ከሱዋል፡፡
እስካሁን በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከ20,000 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ 15 ሚሊዩን በላይ የሚሆኑ ደግሞ እንደተፈናቀሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አኃዛዊ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ነገር ግን በአሜሪካ የሚገኙ ተመራማሪዎች የሟቾች ቁጥር እስከ መቶ ሰላሳ ሺ እንደሚደርስ ይገምታሉ ያለው አልጀዚራ ነው፡፡
ገነነ ብርሃኑ
ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም
