በቴሌግራም በሚላኩ ያልታወቁ ሊንኮችንና ማስታወቂያዎች አማካኝነት ግለሰቦች ለሳይበር ጥቃት እየተጋለጡ ነው ተባለ።

በራሚ ባንክ ቺፍ ኢንፎርሜሽን ሲይስተም ኦፊሰር መሃዲ አሊዬ፤የሰው ሰራሽ አስተውሎት እየተስፋፋ መሆኑን ተከትሎ የሳይበር ጥቃቶች ውስብስብ እየሆኑ መምጣቱን አስታውቋል፡፡

ባለሙያው አቶ መሃዲ በርካታ ሰዎች የቴሌግራምና የፌስቡክ አካውንታቸው እንደተጠለፈ ወይም ሃክ እንደተደረገ ሲገልጹ ይሰማል ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ጥቃት ለመጋለጣቸው ዋንኛ ምክንያቱ ግለሰቦች የማይታወቁ ሊንኮችንና ያሸልማል የሚሉ ሀሰተኛ ያልተረጋገጡ ማስታወቂያዎችን ዝም ብለው በመክፈታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ሆኖም ጥቃቶቹን ለመከላከል የሚላኩ ማናቸውንም ሊንኮችና ማስታወቂያዎች ከመክፈት በፊት ቆም ብሎ ማሰብ፤የማያውቁት ከሆነም የተሻለ ሰው በጉዳዩ ላይ ማማከር ያስፈልጋል ሲሉም መክረዋል።

ባንኮች እንደ ባንክ ፤የአሰራር ስርዓታቸዉን ማጠናከር እንዲሁም ደንበኞቻቸዉ ከሳይበር ጥቃት እራሳቸውን እንዲጠብቁ ግንዛቤያቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) በኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 7 ሺህ 5 መቶ14 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን ገልፆ ግለሰቦቸ እና ተቋማት ራሳቸውን ከጥቃት እንዲከላከሉ ማሳሰቡም የሚታወስ ነው፡፡

ልኡል ወልዴ

ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *