የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከቦች ሽልማት በሰባት ዘርፍ በልዩ ሁኔታ ሰኔ 19/2017 ዓ.ም ይደረጋል።
ሐሙስ በውድድሩ የመዝጊያ ጨዋታ እለት የስሑል ሽረ እና የኢትዮጵያ መድን የ36ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም የአመቱ ምርጦች ይሸለማሉ።
የአሸናፊው የዋንጫ ፕሮግራምም ይከናወናል ፤ ሙሉ ፕሮግራሙ በሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል።
የሽልማት ዘርፎች
የ2017 የአመቱ ኮከብ ተጫዋች
የ2017 የአመቱ ተስፈኛ ተጫዋች
የ2017 የአመቱ ኮከብ ግብ ጠባቂ
የ2017 የአመቱ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ
የ2017 የአመቱ ኮከብ አሰልጣኝ
የ2017 የአመቱ ምስጉን ዋና ዳኛ
የ2017 የአመቱ ምስጉን ረዳት ዳኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ
ጋዲሳ መገርሳ
ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም
