2 ሺህ 216 የመንግስት ተሽከርካሪዎች መረጃ ወደ  ኤሌክትሮኒክስ አጠቃቀም ቁጥጥር ስርአት እንዲገባ ተደረገ

የመንግስት ተቋማት ተሽከርካሪዎች አጠቃቀም ÷ የግዥ ሂደትና አወጋገድን በተመለከተ የሚባክነው ሃብት ለመቆጣጠር የኢ-ፍሊት ትግበራ ስርአት መጀመሩን ሰምተናል።

የነዳጅ ወጪ መጠየቅና ማስተዳደር ባካተተዉ በዚህ ስርአት እስካሁን የ 2 ሺህ 216 ተሽከርካሪዎች መረጃ ወደ ሲስተም  መግባቱ ተገልፆል።

ይህንን የገለፁት የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ የተቋሙን የበጀት አመት የስራ  አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነዉ።

በተሽከርካሪ ሥምሪትና አጠቃቀም  ለመቆጣጠር እየተተገበረ በሚገኘዉ ስርአት የተቋማቱን ወቅታዊ የትራንስፖርት መረጃ ሪፖርት የሚያደርግ ነዉ ተብሏል።

ተሸከርካሪ ያለበትን ቦታ የማመላከት፣ ከተሽከርካሪ ጥገና እና ነዳጅ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን መከታተል የሚያስችል ስርአት ነዉ።

የባለስልጣኑ ዳይሬክተር በአመቱ  በእቅድ ደረጃ 13 የፌደራል ተቋማት ተለይተው እንደነበር ያነሱ ሲሆን ሆኖም ይዘን መቀጠል የቻልነዉ 12ቱን ተቋማት ነዉ ብለዋል።

በ2018 አመት ሁሉም የመንግስት የዩንቨርስቲ ተቋማት በዚህ የኢ-ፍሊት ቁጥጥር ስርአት ዉስጥ እንዲገቡ የሚያስገድድ እንደሆነ ተነግሯል

በ2018 አመት ሁሉም የመንግስት የዩንቨርስቲ ተቋማት በዚህ የኢ-ፍሊት ቁጥጥር ስርአት ዉስጥ እንዲገቡ የሚያስገድድ እንደሆነ ተነግሯል

በመሆኑም ከሀምሌ 1 ጀምሮ ወደ ስራ የገቡት 12 የፌደራል ተቋማት በማንዋል መስራት እንደማይችሉ ገልፀዋል።

በቀጣዩ የተቋሙ በጀት አመት በዚህ የኢ-ፍሊት ማኔጅመንት የተሰኘ ትግበራን በ60 ተቋማት ላይ ለመተግበር እቅድ መያዙን ባለስልጣኑ አሳዉቋል።

ቁምነገር አየለ

ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *