ትግራይ ክልል 7ኛው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ የምታስተናግድ ይሆናል።
ትናንት በጅማ በተደረገው ምርጫ 7ኛው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ትግራይ ክልል እንድታስተናግድ ተመርጣለች።
በዚህ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የትግራይ ክልል ተወካይ ስፖርት ለአንድነትና ለሰላም ትልቅ መሳርያ ነው ብለው ዝግጅቱን ለማድረግ ሙሉ ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።
የትግራይ ክልል ከጅማ የወሰደውን ልምድ በመጠቀም ከባለሙያ ጀምሮ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ውድድሩን እንደሚያዘጋጁ የክልሉ የውድድርና ተሳትፎ ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ብስራት ገልጸዋል።
ለዝግጅቱ መቀሌ ዩኒቨርስቲ ፣ መቀሌ ስታዲየም እና በከተማው የሚገኙ የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎችን በመጠቀም የደመቀ ውድድር ለማድረግ ከወዲሁ ዝግጅት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከሰኔ 10፣ 2017ዓ.ም ጀምረሸ ሲካሄድ የቆየው 6ኛው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ በዛሬው ዕለት በእግር ኳስ ፍፃሜ በሁለቱም ፆታ ኦሮሚያ ክልልና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጨዋታ ፍፃሜውን የሚያገኝ ይሆናል።
ጋዲሳ መገርሳ
ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም
