የክሮሺያ ድንቅ ተጫዋች እና ከባርሴሎና ጋር የሶስትዮሽ ዋንጫ አሸናፊው ኢቫን ራኪቲች በ 37 አመቱ ከእግር ኳስ ማግለሉን አስታውቋል።
ኢቫን ራኪቲች ኢግር ኳሰን የጀመረው ከባዝል የወጣቶች ቡድን ሲሆን ከስዊዘርላንዱ ከለብ ወደ ሻልክ ከመሄዱ በፊት ለዋና ቡድን መጫወት ቸሏል።
በ2014 ባርሴሎና እሱን ለማስፈረም ከመወሰኑ በፊት ወደ ላሊጋው ከለብ ሲቪያ ተዛወረ። ከስድስት አመት በኋላ ወደ ሲቪያ የተመለሰ ሲሆን ከዚህም በሳዑዲ ፕሮ ሊግ ለአልሸባብ የአጭር ጊዜ ቆይታም ነበር ከዚህም ወደ ትውልድ አገሩ ተመለሶ ለሀጅዱክ ስፕሊት ተጨውቶዋል ።
ባለፈው የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው 39 ጨዋታዎች ሁለት ግቦችን እና አምስት አሲስቶችን አስመዝግቧል።
ክሮሽያዊው አማካይ ራኪቲች በእግርኳስ ህይወቱ 17 ዋንጫዎችን በማሳካት ስኬታማ የተጫዋችነት ጊዜን ማሳለፍ ችሏል።
ተጨዋቹ 993 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን 297 የግብ ተሳትፎ ማድረግም ችሏል።
ኢቫን ራኪቲች በኢግር ኳሰ ህይወቱ አራት ላሊጋ፣ አንድ ሻምፒዮንስ ሊግ፣ አንድ ሱፐር ካፕ፣ አራት ኮፓ ዴል ሬይ፣ ሁለት የስፔን ሱፐር ካፕ፣ አንድ የጀርመን ዋንጫ፣ አንድ የስዊዝ ካፕ እና አንድ የፊፋ የአለም ዋንጫን አንስቷል።
ጋዲሳ መገርሳ
ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም
