ቴክሳስ ውስጥ በደረሰዉ የጎርፍ አደጋ ህይወታቸዉ ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ1መቶ በላይ መሻገሩ ተገለጸ፡፡

ባለፈዉ ዓርብ በማዕከላዊ ቴክሳስ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1መቶ የተሻገረ ሲሆን፤ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ሰዎች ያሉበት አልታወቀም ተብሏል።

በአከባቢው ያለው ከባድ ዝናብ እና ነጎድጓድ የነብስ አድን ስራተኞች የወንዝ ዳርቻዎች ዙሪያ የሚያደርጉትን ፍለጋ ከባድ አድርጎባቸዋል ነዉ የተባለዉ።

ሁኔታዉ በዚህ ከቀጠለ ከ4 ቀናት በኋላ በሕይወት የሚገኝ ላይኖር እንደሚችልም የአከባቢዉ ባለስልጣናት ገልፀዋል።

የክርስቲያን ሴቶች አገልግሎት መስጫ ካምፕ እንዳስታወቀው፤ በአገልግሎት ላይ የሚገኙ 27 ሴቶች እና ሰራተኞች በአደጋው የሞቱ ሲሆን፤ ተጨማሪ 10 ሴቶች እና የካምፑ አማካሪ ገና እንዳልተገኙ ገልጿል፡፡

የትራምፕ አስተዳደር በበኩሉ በብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት ላይ ያደረገው የበጀት ቅነሳ አደጋውን ለመከላከል የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንደማይጎዳ አስታዉቋል፡፡

በጎዳላፕ ወንዝ እስካሁን በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት 56 ወጣቶች እና 28 ሕፃናት ህይወታቸዉ ማለፉ የተረጋገጠ ሲሆን፤ 22 ወጣቶች እና 10 ሕፃናት አለመገኘታቸዉን የአሜሪካ ፖሊስ ቢሮ አስታዉቋል ሲል ሮይተርስ አስነብቧል፡፡

ኤርሚያስ ገረመዉ

ሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *