የአሜሪካ አየር ማረፊያዎች በደህንነት ፍተሻዎች ወቅት ጫማ ማውለቅን ሊያስቀሩ ነው

የዩናይትድ ስቴትስ አየር ማረፊያዎች በትራንስፖርት ደህንነት አስተዳደር (TSA) በሚካሄዱ የደህንነት ፍተሻዎች ወቅት ተሳፋሪዎች ጫማቸውን እንዲያወልቁ የሚያስገድደውን እና ከ20 ዓመታት በፊት ገደማ የተጀመረውን ብዙም ተቀባይነት የሌለውን ፖሊሲ ሊያስቆሙ ነው።

የሃገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊ ክሪስቲ ኖውም ምንም እንኳን “ተከታታይ” የፍትሻ ሂደቱ እንዳለ ቢቆይም ለውጡ በመላው የአሜሪካ አየር ማረፊያዎች ላይ ወዲያውኑ ተግባራዊ ሆኗል ብለዋል ።

መንገደኞች አሁንም ቀበቶዎችን እና ካፖርቶችን ማውለቅ እንዲሁም ላፕቶፖችን እና ፈሳሾችን ከቦርሳ ማውጣት አለባቸው፣ ነገር ግን እነዚህም ሂደቶች እየተገመገሙ ናቸው ሲሉ ኖውም ተናግረዋል።

አየር መንገድ ተሳፋሪዎች ለምርመራ ጫማ እንዲያወልቁ የሚጠይቀው መስፈርት በአገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ መሆን የጀመረው እ.አ.አ ከ2006 ጀምሮ አንድ እንግሊዛዊ ወደ ማያሚ በሚጓዝ በረራ ላይ በአንዱ ጫማው ውስጥ ቦምብ ከደበቀ በኋላ ነበር።

ኖውም ማክሰኞ ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “የእኛ የደህንነት ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ሁኔታ ተቀይሯል፣ ተሻሽሏል። የትራንስፖርት ደህንነት አስተዳደር ተለውጧል” ብለዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *