እንደ ሀገር ከታቀደው 7.5 ቢልዮን ችግኞች ውስጥ በአዳማ ከተማ 1.2 ሚሊዮን ያህሉ እንደሚተክል ተገለፀ

በከተማዋ ላለፉት ዓመታት በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል ተብሏል፡፡

ይህ የተገለፀው “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ቃል የኦሮሚ ህብረት ስራ ባንክ ከ3 ሺህ በላይ ችግኞችን የመትከል ዘመቻውን በአዳማ ከተማ ባከናወነበት ወቅት ነው፡፡

የኦሮሚ ህብረትስራ ባንክ ሃምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ባስጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ወቅት የባንኩ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደርበው አስፋው፣ ምናልባት እንደ ባንክ ለህብረተሰቡ ፋይናንስ በማቅረብ ኢኮኖሚውን መገንባት ይቻላል ይሆናል፤ ነገር ግን እፅዋትን ዛሬ በሚገባው ልክ መትከል፣ መንከባከብ እና ማሳደግ ካልተቻለ፣  ሰርቶ መለወጥ ቀርቶ ለመኖርም አዳጋች ነው ሲሉ ገልፀዋል።

እጸዋት ለሰው ልጅ ምግቡ፣ ውበቱ ፣ ኦክሲጅኑ፣  የኢንዱስትሪ ግብዓት ነው በማለት ያለ እፀዋት መኖር እንደማይታሰብ የባንኩ ስራ አስፈፃሚ አስታውሰዋል፡፡

ባንኩ በትኩረት ከሚሰራባቸው ዘርፎቸ መካከል አንዱ ግብርና መሆኑን ገልፀው፣ የአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብሩ የዚህ አካል ነው ብለዋል።

እንደ ሀገር 7.5 ቢልዮን ችግኞችን ለመትከል በታቀደው እንቅስቃሴ ላይ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የመጀመሪያውን ምዕራፍ ከ3 ሺህ በላይ ችግኞችን በመትከል ዘመቻውን በይፋ ተቀላቅሏል ።

በዚሁ ወቅት የአዳማ ከተማ፣ የአባገዳ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት  አቶ ዲመኑ ተሾመ ባደረጉት ንግግር በከተማዋ  1.2 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን ገልፀዋል፡፡

በከተማዋ ላለፉት ዓመታት በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በርካታ ሰኬቶች ተመዝግበዋል ያሉት ስራ አስፈፃሚው፣ ዘንድሮም ለምግብነት፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓት፣ ለከተማ ውበትና ለሌሎችም አገልግሎቶች የሚውሉ ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ ስለመያዙ አንስተዋል፡፡

ልዑል ወልዴ

ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *