የወወክማ ዋና ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ በዛብህ የወጣቶችን የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መጀመረን አስመለክቶ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በዚህም በዘንድሮዉ ብዙ ስራዎችን ለመስራት መዘጋጀታቸዉን ገልጸዋል ።
ዋና ዳይሬክተሩ በዘንድሮው አመት ከሃምሳ ያላነሱ ወጣቶች በክረምተ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እንደሚሳተፉ ነግረውናል፡፡
የዚህን ክረምት የበጎ ፍቃድ ልዩ የሚያደረገው በክረምቱ ብዙ ወጣቶች ቤታቸው ስለሚሆኑ ሁሉንም በአንድ ለማሰባሰብም እንደሚረዳም ነግረውናል፡፡
ወወክማ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የአፍሪካ ሃገሮችመ ስራ እንደሚሰራ የተነሳ ሲሆን፤ ወጣቶች የወወከማን መርህ ካወቁ በኅላ ተቀጥረው እንዲሰሩ እድል እንደሚያመቻችም ነግረውናል፡፡
ድርጅቱ በተለይም ከተቋቋመበት አላማ አኳያ፤ ለብዙ ወጣቶች የስራ አድል የፈጠረ እና ብዙ ወጣቶችንም በአእምሮ አንዲሁም በአካል ብቁ እንዲሆኑ አንደሚያስቸልም ተነስቷል፡፡
ወወክማ በኢትዮጵያ ምስረታወን ካደረገ 75 አመታትን ያስቆጠረ እንደሆነ እና በአዲስ አበባ እንዲሁም በክልልም ባሉት ቅርንጫፎች ወጣቶችን ብቁ የማድረግ ስራ እየሰራየሚገኝ ተቋም መሆኑን ተመላክቷል፡፡
ለዓለም አሰፋ
ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም
