የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከጥቅምት ጀምሮ 2.8 ሚሊየን ነዋሪዎችን ለፋይዳ መታወቂያ መዝግቤያለሁ ብሏል፡፡
በህዝብ በርካታ ቅሬታ እየቀረበበት ያለውን በስራ ላይ የሚገኘዉን የኤጀንሲዉን ሲስተም ለመተካት እየተሰራ ነዉ፤ በጥቂት ወራት ዉስጥም ወደ ስራ ይገባል ሲል ገልጿል፡፡
በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት በመዲናዋ የሚከሰቱ የተለያዩ ኩነቶችን ለመመዝገብ ከተያዘዉ ዕቅድ ዉስጥ 89 በመቶዉን ማሳካት መቻሉም ነዉ የተገለጸዉ፡፡
የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ለመስጠት በዕቅድ ከተያዙ ከ7መቶ ሺህ በላይ ነዋሪዎች ዉስጥ ከ5መቶሺህ በላይ ለሚሆኑት አገልግሎቱን መስጠት መቻሉ በሪፖርት ተገልጿል፡፡
ከተሰጠዉ የነዋሪነት መታወቂያ ውስጥ ከ99 በመቶ በላይ የሚሆነዉ ዲጂታል ሲሆን፤ ቀሪው ለ2 ሺህ 7መቶ74 አቅመ ደካማ እና አሻራ መስጠት ለማይችሉ ነዋሪዎች የተሰጠ የወረቀት አገልግሎት ነው ተብሏል።
በህዝብ በርካታ ቅሬታ እየቀረበበት ያለውን በስራ ላይ የሚገኘዉን የኤጀንሲዉን ሲስተም ለመተካት እየተሰራና በጥቂት ወራት ዉስጥም ወደ ስራ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ሐምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም
