በጥቅምት ወር ላይ ለሚካሄደው የካሜሩን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 81 እጩዎች እንደሚወዳደሩ ተገለጸ

በቅርቡ የስልጣን ሽግሽግ ያደረጉትን ፖል ቢያን ለመፎካከር 81 እጩዎች በተቀመጠው ቀነ ገደብ ለካሜሩን ምርጫዎችን የማደራጀት ኃላፊነት ለተሰጠው ብሄራዊ አካል አመልክተዋል።

ከተወዳዳሪዎቹ መካከል ብዙዎቹ ለሁለተኛ ጊዜ የሚወዳደሩ ሲሆን፤ የተወዳዳሪዎቹ ብዛትም ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል።

በቅርቡ የፖል ቢያን አስተዳደር መደገፍ ያቆሙት ቤሎ ቡባ፤ በፖለቲካ ህይወታቸው ለሁለተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ይወዳደራሉ።

ማመልከቻውን ካስገቡ 81 ተወዳዳሪዎች መካከል በአብዛኛው ወንዶች ሲሆኑ ፤7 ሴቶች ብቻ ይገኙበታል ።

በወንዶቹ መካከል በሚደረገው ፉክክር በእድሜ ትልቁ መሪ ፖል ቢያ ዝርዝሩን ይመራሉ።

ላለፉት አራት አስርት አመታት ስልጣን የያዙት የ92 አመቱ አዛውንት፤ ጤንነታቸው እና ሀገሪቱን የመምራት አቅማቸውን በተመለከተ ስጋቶች እየጨመሩ ቢሆንም ዳግም ለስልጣን ለመወዳደር ያላቸውን ፍላጎት በቅርቡ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

አንዳንድ የአካባቢው ሚዲያዎች እንደዘገቡት፤ የእጩዎች ቁጥር እየጨመረ መሄዱ የህዝቡ የፖለቲካ ለውጥ ፍላጎት እንዲሁም የካሜሩን የፖለቲካ ምህዳር መፍረስን ሊያመለክት እንደሚችል ግምታቸውን ገልጸዋል፡፡

የእጩዎች የመጨረሻ ዝርዝር ከምርጫው 60 ቀናት በፊት የሚታወቅ ይሆናል።

ኤርሚያስ ገረመዉ

ሀምሌ 15/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *