ወደ ትግራይ ክልል የሚገባዉ ነዳጅ ከሁለት ቦቴ አይበልጥም ተባለ

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የትግራይ ክልል ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተኸልሽ ገ/ህይወት፤ ወደ ክልሉ የሚገባዉ ነዳጅ ከሁለት የጭነት ቦቴ እንዳይበልጥ በመደረጉ እንደ ክልል ከፍተኛ ችግር ዉስጥ መግባታቸዉን ገልፀዋል።

ከጦርነቱ በፊት ይገባ የነበረው ነዳጅ መጠን በቀን ከ8 እስከ 16 ቦቴ እንደነበረ አስታዉሰዋል፡፡

በዚህ ምክንያት አሁን ላይ 72 ማደያዎች ስራ ማቆማቸዉንም ተናግረዋል።

በዚህም ምክንያት በአሁን ሰዓት በትግራይ ክልል ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ሰፊ ችግር እየገጠመዉ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የነዳጅ ችግር እንዲፈታ ለሚመለከታቸዉ የፌደራል አካላት ደብዳቤ መላክን ጨምሮ በአካልም በተደጋጋሚ እየተጠየቀ መሆኑንና እስካሁን ግን ምንም አይነት ምላሽ እንዳልተሰጣቸዉ አንስተዋል፡፡

የሚመለከታቸዉን አካላት ወደ አዲስ አበባ በመላክ ከአንድ ወር በላይ ንግግር ቢደረግም ምንም መፍትሄ ማግኘት አልቻልንም ብለዋል፡፡

ወደ ተፈናቃዮች መላክ የነበረባቸዉ ምግብና መድኃኒት በነዳጅ ዕጥረት ምክንያት እየደረሰላቸዉ እንዳልሆነም ገልጸዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሀምሌ 15/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *