የሐረሪ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ በአብዛኛው በክረምት ወራት የሚነሳውን የወባ በሽታ ለመከላከል የአካባቢ ጥበቃና ሌሎች ተያያዝ ስራዎቾ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
የቢሮው ምክትል ሀላፊ ዶክተር ኢማን ዜዳን፤ ለ80ሺህ ዜጎች የጤና በጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የህክምና አገልግሎቱ ነፃ የጤና ምርመራ፣ የደም ልገሳ እና ሌሎች አገልግሎቶችን ያካተተ እንደሆነም ዶ/ር ኢማን ተናግረዋል።
በ2016 ዓ.ም ክረምት ላይ ለ152 ሺህ ዜጎች የጤና በጎ አገልግሎት በመስጠት እንደክልል ከጤና ሚኒስቴር እውቅና እና ሽልማት መረከባቸውን አንስተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ወቅቱን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ እንደ ወባ ያሉ በሽታዎችን ለመከላከል የሚውሉ መድሃኒቶችን በበቂ ሁኔታ እያቀረብን እንገኛለንም ብለዋል።
ልኡል ወልዴ
ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም
