የአረብ ሊግ በጋዛ ሰብዓዊ ቀውስ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ።

የአረብ ሊግ ተወካዮች በጋዛ ባለዉ ጦርነት እና እየተባባሰ ስላለው የሰብዓዊ ቀውስ በካይሮ በአስቸኳይ ስብሰባ አካሂደዋል።

ከሁለት ሚሊየን በላይ የሚሆኑ በጋዛ የሚኖሩ ዜጎችን ህይወት አስቸጋሪ ባደረገዉ ረሃብ ዙሪያ ለመወያየት ልዩ ስብሰባ እንዲደረግ የጠየቀችዉ ፍልስጤም ናት፡፡

የተባበሩት መንግስታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ እንዳለው ከግንቦት ወር መጨረሻ ጀምሮ ከ 1ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በረሃብ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእስራኤል ኃይሎች ባሳለፍነው ሳምንት የምግብ እርዳታ በሚሹ ፍልስጤማውያን ላይ ተኩስ ከፍተዋል ሲል ከሷል።

የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ግዛቱን ወደ ረሃብ አፋፍ ያደረሰው ጦርነት በእርዳታ ፈላጊዎች ላይ ከተፈፀሙት እጅግ የከፉ ጥቃቶች አንዱ ነው ብሏል።

በስብሰባው ላይ የተሳተፉት መሪዎች በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት ለማቆም በእስራኤል ላይ ጫና እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ሀሚድ አብደላ

ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *