ቻይና አሜሪካ ከዩኔስኮ እወጣለሁ ማለቷን አወገዘች

አሜሪካ ከተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ   እወጣለሁ ማለቷን ተከትሎ  ቻይና በጽኑ አውግዛለች።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጓ ጂያኩን የአሜሪካ እርምጃ በአለም አቀፍ ትብብር እና ሃላፊነት ላይ ጉዳት ያደርሳል ብለዋል።

ቃለ አቀባዩ አክለውም ዩኔስኮ እና በርካታ ሀገራት አሜሪካ እንደገና ለመውጣት በወሰነችው ውሳኔ ማዘናቸውንም ገልጸዋል።

አሜሪካ ከዩኔስኮ ስትወጣ ይሄ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑን እና የአባልነት ክፍያዋን ለረጅም ጊዜ እንዳለከፈለች ተነግሯል።

ይህም እንደ አንድ ሃላፊነት እንዳለበት ሀገር የሚመጥን ባህሪ አይደለም መባሉን የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው።

በ ሃሚድ አብደላ

ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *