ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፤ በ2017 ዓ.ም ከባድ ወንጀልን 43 በመቶ በመቀነስ ስጋቶችን መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል።
በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከአምስት ሚሊየን በላይ ሰዎችን በማወያየት የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸዉንም ገልጸዋል።
የፓሊስ ማዕከላት በማሳደግ በኩል ከአራትና አምስት አመት በፊት ከነበሩት 50 የሚሆኑ ፓሊስ ጣቢያዎች፤አሁን ላይ ከ90 በላይ ተደራሽ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡
ህገወጥ ስራዎች የሚሰራባቸዉ እና ለወንጀል ተግባር ሰፊ ድርሻ ያላቸዉን ቦታዎች በመቆጣጠር ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር መሠራቱን አንስተዋል።
ከዚህ በፊት ፓሊስ ስራዎችን ሲሰራ የነበረዉ በተለምዶ እንደነበር የገለጹት ኮማንደር ማርቆስ፤ አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም
