በጥቃቱ ከሞቱት በተጨማሪ በርካቶች መቁሰላቸው ተገልጿል፡፡
የክልሉ መሪ በዛፖርዢያ የተፈፀመው የሌሊት ጥቃት በዙሪያው ያሉ ቤቶችንም አውድሟል ብለዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዋና ፀሃፊ በበኩላቸዉ ጥቃቶቹን ሩሲያ የፈፀመችው ‹‹ሌላ የጦር ወንጀል›› ነዉ ሲሉ አውግዘዉታል።
ዛፖርዢያ ሩሲያ ከ2022 ጀምሮ ወደራሷ ግዛት አካል አድርጋ ከምትቆጥራቸዉ አራት የምስራቅ ዩክሬን ግዛቶች አንዷ ስትሆን፤ በአብዛኛው ግን በዩክሬን ቁጥጥር ስር ትገኛለች።
የዩክሬን የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር፤ እስር ቤት ላይ ጥቃት መፈጸም በሰብዓዊ ህግ ላይ የተፈፀመ ከባድ ጥሰት ነው ብለዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሞስኮ ማሳሰቢያ የሰጡ ሲሆን፤ ሩሲያ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ 10 ወይም 12 ቀናት ብቻ እንደሰጡ እና ካልሆነ ግን ከባድ ማዕቀብ እንደሚጣልባት አስጠንቅቀዋል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።
ሀኒፍ ሀምዛ
ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም
