በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን  የድርቅ ተጋላጭነትን ለመቀነስ እና በምግብ ራስን ለመቻል በዚህ ክረምት 710 ሄክታር መሬት ለእርሻ ይውላል ተባለ።

ዞኑ ለተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት በዚህ ክረምት ከክልሉ 710 ሄክታር መሬት ተቀብሎ ከ4 መቶ ሄክታር በላይ ወደ እርሻ ማስገባቱን የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ፅ/ቤት አስታዉቋል።

የዞኑ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ምህረት መላኩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም  እንዳሉት  ከዚህ ቀደም ከውጭ ድርጅቶች ይመጡ የነበሩ ሰብዓዊ ድጋፎች መቀነሳቸውን አንስተው ይህን በራስ ለመሸፈን ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል።

በዞኑ የሚገኙ ወረዳዎች ምርታቸውን በማሳደግ ፤ 30 በመቶውን ተጋላጭ ማህበረሰብ እንዲደግፉ እና የተቀረውን በክልል፣ በፌደራል እና በግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን ገልፀዋል።

አካባቢው ዝናብ አጠር መሆኑን ያነሱት አቶ ምህረት ከሰሞኑ የተሻለ የዝናብ ሁኔታ በመኖሩ ይህን በመጠቀም ድርቅን መከላከል የሚችል ምርት ለማግኘት ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።

ዘላቂ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅም እንዲኖር በምግብ ራስን መቻል ፋይናንስ እና የምግብ ማዕከል ማቋቋማቸውንም ጠቅሰዋል።

ሐመረ ፍሬው

ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *