በ2017 በጀት ዓመት በ 3 ሺ 4 መቶ 99 የጤና እና መድኃኒት ችርቻሮ ተቋማት ላይ ቁጥጥር ተደርጎ በ309 ተቋማት ላይ በተገኘባችው ችግር ምክንያት አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል ለ2 መቶ 27 ተቋማት ያለባቸውን ችግር እንዲያስተካክሉ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የባለስልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በ76 የጤና ተቋማት፤መድኃኒት ችርቻሮ እና የባህል ህክምና ተቋማት ላይ ደግሞ ጊዜያዊ እሸጋ መደረጉን አንስተዋል፡፡
እንዲሁም 6 ተቋማት ከተፈቀደላቸውና ከተሰጣቸው ብቃት ማረጋገጫ ውጭ ሲሰሩ በመገኘታቸው ምክንያት የብቃት ማረጋገጫቸው እንዲሰረዝ ተደርጓል ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ በ2017 አ.ም ግምታዊ ዋጋቸው ከ74 ሚሊዮን 9 መቶ77 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ጤና አስጊ የሆኑ ፣ የተበላሹ እና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው የመድኃኒት ምርቶች ማስወገዳቸውን አቶ እስጢፋኖስ ገልጸዋል፡፡
ሐመረ ፍሬው
ነሐሴ 1/2017 ዓ.ም
