አዋሽ ባንክ ባለፈው ሐምሌ ወር ለደንበኞቹ ከ125 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማቅረቡ የሚታወስ ነዉ፡፡
ሆኖም ባንኩ ከደንበኞቼ ቀረበልኝ ባለዉ ጥያቄ መሰረት ሁለተኛ ዙር ለሂሳብ ዓመት 2025/26 የነሐሴ ወር ከ1መቶ10 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ለደንበኞቼ እየሰጠዉ እገኛለሁ ብሏል።
ባንኩ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ የሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ የመጠባበቂያ ክምችት ከመሻሻሉ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች በቂ የውጭ ምንዛሪ ከማቅረቡ በተጨማሪ የባንኩ አጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ ግኝት እያደገ ስለመሆኑም ተገልጿል።
ሆኖም በሀገሪቱ ያለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ እና የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት በሚደረገው ጥረት ይህ እንቅስቃሴ አንዱ አካል ነው ተብሏል።
በመሆኑም ማንኛውም የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት የሚፈልግ የባንኩ ደንበኛ መመዝገብና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል ባንኩ አስታዉቋል፡፡
ልኡል ወልዴ
ነሐሴ 1/2017 ዓ.ም
