የአየር አምቡላንስ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ንብረት የሆነ አውሮፕላን ሐሙስ ዕለት ከኬንያ ዋና ከተማ ውጭ በሚገኝ የመኖሪያ አካባቢ መከስከሱን የአውሮፕላኑ ባለቤት አስታውቋል።
አገልግሎት ሰጪው የተጎጂዎችን ቁጥር ወይም ሊከሰት የቻለበትን ምክንያት አልገለጸም፡፡
በሰጠዉ መግለጫ ስለሁኔታው የተሟላ መረጃ ለማረጋገጥ አግባብነት ካላቸው የአቪዬሽን ባለስልጣናት እና የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ሰጪ ቡድኖች ጋር እየተባበርን ነዉ ብሏል፡፡
የኬንያ ቀይ መስቀል ማህበር የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹ አደጋዉ ወደተከሰተበት ከናይሮቢ ጋር ድንበር ወደ ምትጋራው ኪአምቡ ግዛት መጓዛቸውን አስታውቋል።
ቀደም ሲል የኬንያ ቀይ መስቀል ማህበር የተከሰከሰው አውሮፕላን ሄሊኮፕተር መሆኑን ተናግሮ ነበር።
እስካሁን የኬንያ መንግስት ባለስልጣናት በጉዳዩ ዙሪያ ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ አልሰጡም ሲል የዘገበዉ አፍሪካ ኒዉስ ነዉ።
ሀኒፍ ሀምዛ
ነሐሴ 2/2017 ዓ.ም
