የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የክለብ ላይሰንሲንግ የፍትህ አካል (FIB) ክለቦች በካፍ ክለብ ላይሰንሲንግ ኦንላይን ፕላትፎርም (CLOP) ላይ ሲመዘገቡ ያያያዟቸውን ሰነዶች መሠረት በማድረግ በምስሉ ላይ የተጠቀሱ ውሳኔዎችን ማሳለፉን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።
ፌዴሬሽኑ ጨምሮ በውሳኔዎች ላይ ቅሬታ አቅራቢ ክለብ ይግባኝ የመጠየቅ መብቱ እንደሆነና ይህ የውሳኔ መግለጫ በየቀኑ የሚፈጠሩ ለውጦችን በመመርኮዝ ተሻሽሎ ይፋ እንደሚደረግ አመላክቷል።
ማስታወሻ
- በውሳኔዎች ላይ ቅሬታ አቅራቢ ክለብ ይግባኝ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ይህ የውሳኔ መግለጫ በየቀኑ የሚፈጠሩ ለውጦችን በመመርኮዝ ተሻሽሎ ይፋ ይደረጋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
ነሐሴ 5/2017 ዓ.ም
