ቤት አልባ ሰዎች ከዋሽንግተን “በፍጥነት” መውጣት አለባቸው አሉ ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዋሺንግተን ዲሲ የሚታዩ ወንጀሎችን ለመከላከል ቃል ገብተው በከተማዋ የሚገኙ ቤት የሌላቸው ሰዎች “መውጣት አለባቸው” አሉ።

የከተማዋ ከንቲባው ግን ዋይት ሐውስ ዋና ከተማዋን ከባግዳድ ጋር በማነጻጸሩ ተችተዋል።

እሁድ ዕለት በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ “የምትቆዩበት ቦታ እንሰጣችኋለን፤ ነገር ግን ከዋና ከተማው የራቀ ነው” በማለት ለጥፈዋል።

የሪፐብሊካኑ ፕሬዚዳንት ከተማዋን “ከዚህ በፊት ከነበረችው የበለጠ አስተማማኝ እና የበለጠ ውብ” ለማድረግ ስለወጠኑት ዕቅድ ሰኞ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘዋል።

የከተማዋ ከንቲባ ዲሞክራቷ ሙሪየል ቦውሰር “የወንጀል መጨመር እያጋጠመን አይደለም” ሲሉ አስተባብለዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል ።
 

ነሐሴ 5/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *