ሩዋንዳ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፤ ኃይሎቿ በምስራቅ ኮንጎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችን በመግደል ከአማፂያን ጎን ተሳትፈዋል በሚል ያቀረበውን ውንጀላ ‹‹ሀሰት›› በማለት አጣጥላዋለች።
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት የዓይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ እንዳስታወቀዉ፤ የኤም23 አማፂያን በሰሜን ኪቩ ግዛት በሚገኙ አራት መንደሮች ላይ በሐምሌ ወር በፈጸሙት ተከታታይ ጥቃት ቢያንስ 3መቶ19 ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል።
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት፤ አማፂያኑ የሩዋንዳ ጦር ድጋፍ እንደነበራቸው አስታውቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ክሱን ‹‹ተቀባይነት የሌለው››ሲል አውግዟል።
መግለጫው፤ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኤጀንሲን በኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ያለውን ግጭት ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት ለማዳከም እየሞከረ ነው ሲል ያለማስረጃ ከሷል።
በሐምሌ ወር የኪንሻሳ እና የM23 አማፂያን በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ውስጥ ለሳምንታት ከተገናኙ በኋላ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነትን የሚያረጋግጥ የመርህ መግለጫ ቢፈራረሙም፤በግዛቱ ላይ ግጭቶች አሁንም ቀጥለዋል።
በርካታ የተባበሩት መንግስታት ሪፖርቶች ሩዋንዳ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን፣ የጦር መሳሪያዎችን እና የሎጅስቲክስ ድጋፍን ለኤም23 አማፂያን ልካለች ሲሉ ከሰዋል፤ኪጋሊ ግን ክሱን አስተባብላለች።
እስከዳር ግርማ
ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም
