የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ልጅ ትራምፕ በሀገሩ ላይ የጣሉትን ታሪፍ አደነቀ

የቀድሞው የብራዚል ፕሬዚዳንት ዣየር ቦልሶናሮ ልጅ፤ በሀገሩ ላይ ከፍተኛ ቀረጥ የጣሉትን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማድነቅ፤ ብራዚል ላይ ተጨማሪ እርምጃዎች ሊወሰድ እንደሚችሉ አስጠነቀቀ።

ብራዚል ውስጥ ተመራጭ የኮንግረስ አባል የሆነው ኤድዋርዶ ቦልሶናሮ፤ በዋሽንግተን ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ አድርጓል።

ኤድዋርድ በዋሽንግተን በመገኘት የትራምፕ አስተዳደር አባቱን በመፈንቅለ መንግሥት ወንጀል ለፍርድ ያቀረቡ ባለሥልጣናትን እንዲቀጣ ለወራት የጉትጎታ ስራ ሲያከናውን ቆይቷል።

የኮንግረስ አባሉ በግለሰቦች ላይ የሚጣሉ ተጨማሪ ማዕቀቦች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተናግሯል።

“ማዕቀቦችን ተግባራዊ ማድረግ እና በሌሎች ሰዎች ላይ የሚጣሉ የማግኒቲስኪ ማዕቀቦችን ማራዘም የሚያስችል ትልቅ እድል አለ። ለምሳሌ ብራዚልን እያጋጠማት ካለው ተቋማዊ ቀውስ ለማውጣት ከሚያደርጉት ሌሎች ግፊት ማድረጊያ ዘዴዎች መካከል አንዱ የሆነው ቪዛ ማስወገድን የተመለከተ እርምጃ በሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ዴስክ ላይ ይገኛል” ብሏል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሀሙስ በዋይት ሀውስ ባደረጉት ንግግር ብራዚልን መጥፎ የንግድ አጋር እንደሆነች በመጥቀስ ከስሰዋል። አሜሪካ ከብራዚል ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ጉድለት እንዳለ በማንሳት ስህተት ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመት አሜሪካ ከብራዚል ጋር ባደረገችው ንግድ 7.4 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ትርፍ ተመዝግቧል።
“በእውነቱ ቦልሶናሮ ላይ ለማድረግ እየሞከሩ ያሉት የፖለቲካዊ ግድያ ነው። ይህ በጣም መጥፎ ነው ብዬ አስባለሁ” ሲሉም ዣይር ቦልሶናሮን ተከላክለዋል።

የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት የተከሰሱት በ2022 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፏቸውን ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ስልጣኑን እንዳይይዙ ለማድረግ መፈንቅለ መንግሥት አሲረዋል በሚል ነው።

ቦልሶናሮ መንግሥትን ለመገልበጥ ሙከራ አድርገዋል የሚለውን ውንጀላ ቢያጣጥሉም፤ በምርጫው የደረሰውን ሽንፈት ለመቀልበስ በተደረጉ ስብሰባዎች ላይ መሳተፋቸውን አምነዋል።

ፍርድ ቤቱ በቀጣዮቹ ሳምንታት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ነሐሴ 9/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *