በዛሬዉ እለት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን የ2017 አ.ም በጀት አመት ስራዎች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
አገልግሎቱ የኢነርጂ ቆጣሪዎችን ቤት ለቤት ለመመርመር አቅዶ 3.1 ሚሊዮን በላይ መመርመር መቻሉን ተናግሯል።
የሀይል ስርቆት ፈፅመዋል የተገኙ ከአንድ ሺህ በላይ ግለሰቦችን ተጠያቂ ማድረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልፆል።
የሀይል ብክነትን ለመከላከል እና ለመቀነስ አገልገሎቱ ስራዎች እንደነበሩት የገለፁት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ ተናግረዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ነባር ቆጣሪዎችን በዘመናዊ ስማርት ቆጣሪዎች የመተካት ስራ አንዱ እንደነበር አንስተዋል።
በበጀት አመቱ ማገባደጃም 53 ሺህ 714 ስማርት ቆጣሪዎች ወደ አገልግሎት ገብቷል ሲል አገልግሎቱን ተናግሯል።
ድንገተኛ የመደበኛ የቆጣሪ ምርመራ ስራዎች እንደሚሰራ የተናገሩት የአገልግሎቱ ስራ አስፈፃሚ ከስማርት ሜትር ዳታ ቤዝ በተገኙ መረጃዎች ስርቆት ፈፅመዉ የተገኙ ደንበኞች እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።
ተቋሙ ከ5 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንዳሉት የገለፀ ሲሆን 4.2 ሚሊዮን በላይ የድህረ ክፍያ፣ ከ9 መቶ ሺህ በላይ የቅድመ ክፍያ እና 43 ሺህ በላይ የስማርት ሜትር ተጠቃሚ ደንበኞች መሆናቸዉ ነዉ የተገለፀዉ
በሌላ በኩል በበጀት ዓመቱ ከዋናው ግሪድና በሚኒ ግሪድ ወይም ከፀሐይ ኃይል በአጠቃላይ 155 የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ከጋዜጣዊ መግለጫው ሰምተናል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከኃይል ሽያጭ እና ከሌሎች ልዩ ልዩ ገቢዎች 63 ነጥብ 12 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጌቱ ገረመው ተናግረዋል ።
ቁምነገር አየለ
ነሐሴ 9 /2017 ዓ.ም
