የካናዳ አየር መንገድ የበረራ ሰራተኞች ስራ የማቆም አድማ ለማድረግ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተከትሎ አየር መንገዱ በረራዎችን መሰረዝ መጀመሩ ተሰምቷል።
በዚህም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መንገደኞችን ጉዞ ሊያስተጓጉል ይችላል ተብሏል።
የካናዳ አየር መንገድ ሙሉ በሙሉ መዘጋት በየቀኑ በግምት 130ሺ ተጓዦችን መጉላላት ላይ ይጥላል ተብሏል።
ወደ 300 የሚጠጉ የበረራ አስተናጋጆች የ ስራ ገበታቸው ላይ እንዳልትገኙና በዚህም በረራዎች እንደተሰረዙበት አየር መንገዱ በ ኤክስ ድረገፁ ላይ ፅፏል።
የኤር ካናዳ ዋና ኦፕሬሽን ኦፊሰር ማርክ ናስር አየር መንገዱ የኤር ካናዳ እና የኤር ካናዳ በረራዎችን በከፊል ማገድ መጀመሩን አስታውቀዋል።
በቅዳሜ ማለዳ ሁሉም በረራዎች ይቆማሉ ሲሉም ሃላፊው ተናግሯል።
የአድማው ምክኒያት እስካሁን በግልፅ አልተቀመጠም ዘገባው የአናዱሉ ነው፡፡
ገነነ ብርሃኑ
ነሐሴ 9/2017 ዓ.ም
