የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፀጥታ ችግር ባለባቸዉ አካባቢዎች የወደሙ መሠረተ ልማቶች መልሶ ለመገንባት በባለፉት ሁለት እና ሶስት አመታት እንደተፈተነ ገልፆል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ ይህንን የገለፁት የተቋማቸዉን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረበብበት ወቅት ነዉ።
በቢሊየን የሚቆጠር ወጪዎች ፈሰስ በማድረግ በግጭቶቹ ምክንያት የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለማልማት ስራ መሠራቱን ዋና ስራ አስፈፃሚ ገልፀዉ ቀሪ አካባቢዎች ላይ በቀጣይ የሚታይ እንደሚሆን አንስተዋል።
ከዚህ ባለፈ በልማት ተነሳሺነት እና ሌሎች ሁኔታዎች በከተማዋ ራቅ ብለዉ በሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የግል ቆጣሪ አቅርቦት ላይ ቅሬታ እየተነሳ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ ይገለፃል።
የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመዉ ይህንን ቅሬታ መሠረት አድርገዉ ምላሽ ሰጥተዋል።
በምላሻቸውም አገልግሎቱ ቆጣሪ ያስቀመጠባቸዉ ሆኖም የዉስጥ ለዉስጥ የመስመር ዝርጋታ ጋር መዘግየቶች እንዳሉ ተናግረዋል።
የሲቪል ስራዉን ከሚሰራዉ አካል ጋር በጋራ በመሆን ችግሩን ለማስተካከል እንደሚሞከር ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኤሌክትሪክ ተደራሽነት በሀገሪቱ ካለዉ የህዝብ ቁጥር አንፃር ጋር በንፅፅር ሲታይ የሚቀረዉ እንደሆነ ተገልፆል።
ለዚህ ደግሞ የአገልግሎቱ የፋይናንስ ችግርን እየጠቀሰ ይገኛል።
በአሁን ወቅት 25 ሚሊዮን ያህሉ እማወራዎች እና አባወራዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚጠበቅ ቢሆንም ተቋሙ ተደራሽ መሆን የቻለዉ ለ5.1 ሚሊየን ለሚሆኑት ብቻ መሆኑንም ከመድረኩ ሰምተናል።
ቁምገር አየለ
ነሐሴ 16 /2017 ዓ.ም
