የኢትዮጲያ አየር መንገድ Leap-1b የተሰኘ የአውሮፕላን ሞተርን በተሳካ ሁኔታ ማምረቱን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ይህንን Leap-1B Engine PRSV1 የተሰኘ ዘመናዊ የአውሮፕላን ሞተር በማምረት ስኬታማ ስራ መስራቱን አየር መንገዱ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ይህ ውጤት ለኢትዮጲያ ኩራት ነው ሲሉ ገልፀውታል።

ይህ ሊፕ-1ቢ የተሰኘው የአውሮፕላን ሞተር ጥገና አቪዬሽኑ ከገነባው እና ማምረት ከሚችላቸው ስራዎቹ መካከል አንዱ ያደርገዋል ብለዋል።

አገልግሎታችንን እያሳደግን እና አቅማችንን እያሰፋን ያለንበት ወቅት ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ መስፍን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን
በታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ላይ መድረሱን ማሳያ ስራ ሰርቷል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የተለያዩ የአሮፕላን ክፍሎችን እንደ የሞተር ጥገና፣ የአውሮፕላኑ የአካል ክፍሎች ጥገና፣ የተለያዩ የምህንድስና አገልግሎቶች፣ እና ሌሎችንም የጥገና መሳሪያዎች በማምረት ለቦይንግ ካምፓኒ የማቅረብ አቅም ላይ መድረሱን አየር መንገዱ ለኢትዮ ኤፍኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል።

የኢትዮጲያ አየር መንገድ እጅግ ዘመናዊ የአውሮፕላን ጥገና ወርክሾፕን ጨምሮ ፥ ዘመናዊ መጋዘንን በቅርብ ማስመረቁ ይታወሳል።

የውልሰው ገዝሙ

ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *