ለሚሰጡት አገልግሎት ጉቦ የጠየቁ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የቄራዎች ድርጅት የሚሰጠውን አገልግሎት ለማግኘት የሄዱ ተገልጋዮችን ገንዘብ የጠየቁ ሁለት ተጠርጣሪ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የከተማዋ ከንቲባ ጽ/ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስነበበው 1ኛ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰይድ እንድሪስ ከማል እና 2ኛ ምክትላቸው አቶ ዮሴፍ ድሪብሳ ማሞ ገንዘብ ካላመጣችሁ አገልግሎት አታገኙም በማለት ፤ እንግልት ሲፈጠሩ ቆይተው በደረሰ ጥቆማ በትላንትናው ዕለት ከተገልጋይ ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ሕብረተሰቡ እንዲህ አይነት የሙስና ተግባራትን ሲመለከት ለከንቲባ ጽ/ቤት ጥቁማ እንዲሰጥም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *