ለ75 እማወራና አባወራ 33  ሚሊዮን ብር ኢንቨስት በማድረግ የስራ እድል መፍጠሩን ሄኒከን ኢትዮጵያ አስታወቀ

ሄኒከን ኢትዮጵያ በሸገር ከተማ ኮዬ- ፈቼ እና በቂሊንጦ ለሚገኙ 75 አባወራና እማወራ የኑሮ ማሻሻያ እና የድጋፍ ፕሮጀክት በዛሬው እለት  አድርጓል።

የሄኒከን ኢትዮጵያ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ዊሊየም ባርት ፤ “ከማህበረሰቡ ለማህበረሰቡ” በሚል መሪቃል የማህበረሰቡን ህይወት በዘላቂነት ሊያሻሽሉ የሚችሉ ከስልጠና ጀምሮ፣የግብዓትና የገንዘብ እርዳታ አድርገናል ብለዋል።

ሆኖም 75 እናቶች እና አባቶች እንዲሁም ወጣቶች በመረጡት ሙያ ላይ እንዲሰማሩ ተደርጓል ያሉት ዳይሬክተሩ በአምስት ቡድ ተከፍለው ወደ ስራው መሰማራታቸውን ነው የገለፁት።

ከነዚህ መካከል በእንጀራ መጋገር ንግድ፣በዶሮ እርባታ፣በወተት ላም፣በከብት እርባታና በባልትና  ውጤቶች ዘርፍ ወደ ስራው መግባታቸውን ነው የተናገሩት ።

በሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጨ ክ/ከተማ ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ቶላ ወርቅ ፤እነዚህ ሰዎች እራሳቸውን ብቻ ሳይሆን በዓከባቢው ላይ ያሉትን ሌሎች ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ብለዋል።

የእድሉ ተገቃሚዎችም ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።

ልኡል ወልዴ

ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *