በሬክተር ስኬል 6.0 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ምስራቅ አፍጋኒስታንን መምታቱ ተገልጿል፡፡
ቢቢሲ ባለስልጣናት ነገሩኝ እንዳለዉ ከሆነ፤ ቢያንስ 20 ሰዎች ሞተዋል፤ከ1 መቶ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዉ በሆስፒታሎች ውስጥ የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸዉ ነዉ ብሏል፡፡
በደርዘን የሚቆጠሩ ቤቶች በፍርስራሽ ስር እንደሆኑ የዘገቡት የታሊባን መንግስት ምንጮች፤ የሟቾች ቁጥር ከፍ ሊል ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን አስታዉቀዋል።
የታሊባን መንግስት ባለስልጣናት፤ በተራራማ አካባቢዎች የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ መጥለቅለቅ በመኖሩ ሰብዓዊ ድርጅቶች በአየር ብቻ ተደራሽ በሆኑ አካባቢዎች የማዳን ስራ እንዲያካሂዱ አሳስበዋል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጡ ከካቡል እስከ ፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ ከ3መቶ ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ላይ የሚገኙ ሕንፃዎችን አናውጧል ሲል የዘገበዉ ቢቢሲ ነዉ።
እስከዳር ግርማ
ነሐሴ 26/2017 ዓ.ም
