የG7 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪያቸውን አቅርበው፤እስራኤል የሰብአዊ እርዳታ እንዲደረግ መፍቀድ አለባት ብለዋል።
ሚኒስትሮቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ፤በጋዛ በቂ የሆነ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረግ፣በሲቪሎች ላይ የሚደርሰው መጠነ ሰፊ ስቃይ እንዲቃለል እንዲሁም ሁሉም ታጋቾች እንዲፈቱ በማድረግ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲኖር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ሀማስ በጥቅምት 7 2023 ያደረሰውን ጥቃት አውግዘናል፤ሃማስ በጋዛ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ምንም አይነት ሚና እንደማይኖረው እና ለእስራኤል ስጋት መሆን እንደሌለበት ደጋግመን ተናግረናል ብለዋል።
በጋዛ መልሶ ግንባታ ላይ ወደፊት የሚኬድበትን መንገድ ለመቅረጽ እና የእስራኤል-ፍልስጤምን ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር በአረብ አጋሮች በቀረቡ ሀሳቦች ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን ብለዋል ሲል የዘገበዉ አልጀዚራ ነው።
ሀና ሰይፉ
መስከረም 14/2018 ዓ.ም
